Nehodí se? Vůbec nevadí! Zboží můžete vrátit až do 30 dní
S dárkovým poukazem nešlápnete vedle. Obdarovaný si za dárkový poukaz může vybrat cokoliv z naší nabídky.
Až 30 dní na vrácení zboží
"የተራቡ የእግዚአብሔር ማዕደኞች" የተባለው ይህ መጽሐፍ እ.ኤ.አ በ2026 የተጻፈና የታተመ ነው። ይህን መጽሐፍ የጻፍኩበት ዋና ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የደረሰብንን አደገኛ መንፈሳዊ ረሀብ ለማሳየት ነው። እንዲሁም ከሰማይ የሚመጣው የእግዚአብሔር ማዕድ ምን ማለት እንደሆነ፣ ማዕዱን የምንለይበት መንገድ፣ ማዕዱ በምድር ላይ የሚያከናውነው ተግባር ምን እንደሚመስል ከእግዚአብሔር የዘላለም አጀንዳ ጋር በማያያዝ በጥልቀት የተጻፈ ነው። በተጨማሪም አምስቱ የክርስቶስ ስጦታዎች በእግዚአብሔር ማዕድ ክርስቶስ በምድር ይሠራ በነበረበት የአላፊነት ክብደት ልክ ቀልድ የሌለውን ሥራ እንዲሠሩ የተጠሩ ናቸው። ታዲያ፦ ይህ ነው የማይባሉ በቊጥርም በዓይነትም ብዙ የተማሩ የነገረ መለኮት ምሁራን በየዘርፉ እያሉን ስለምን ተራብን? ስምን የተላበሱና የገነኑ ሐዋርያትና ነቢያት እያሉን እንዲት ልንራብ እንችላለን? ጥቅስን ከጥቅስ ጋር እያገናኙ የሚያስተምሩን ብዙ አስተማሪዎች በየስፍራው እያሉን ለምን በመንፈሳዊ ረሀብ ውስጥ ወደቅን? ለመንጎቻቸው የሰማዩን ምግብ እንዲመግቡ የተሾሙ እረኞች በየአጥቢያው እያሉን ለምን ጠኔ ያዘን? ለምን የእውነተኛው መንፈሳዊ ምግብ ጣዕም ጠፋብን? ሕዝቡን እናነቃቃለን በሚል አሳብ በብዙ ዋጋ አሉ የተባሉትን መዘምራንና የቃሉን አገልጋዮች በተደጋጋሚ ጋብዘን ለምን የሕዝቡ ረሀብ እየጨመረ መጣ? እኛም እንደ አይሁድ አለቆች በብዙ እውቀት የተሞሉ "የአብያተ ክርስቲያን ኅብረት" የሚባል ሸንጎ አለን፣ ጥያቄው፦ ይህ ሸንጎ ወይም ኅብረት እንደ ሐዋርያቱ ዘመን ሸንጎ ለሕዝቡ መንፈሳዊ ጥጋብን ያላመጣበት ምክንያት ምንድን ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች የሚመልስ መጽሐፍ ነው።
Ahoj! Jsem Libroamiko, tvůj knižní rádce.
Jak ti můžu pomoct?